የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ ቤተሰቦች ሐምሌ 26 ቀን፣ 2012 ዓ.ም ሁለተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስመልክቶ ለተደረገው ሃገራዊና ተቋማዊ ጥሪ ምላሽ በመስጠት፣ በአዲስ አበባ ሳሪስ አዲሱ ሰፈር በሚገኝ ጥብቅ የደን ልማት ቦታ ተገኝተው በርካታ ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
በተጨማሪም ለሠልጣኞች እና ለአካዳሚው ማህበረሰብ አረንጓዴ፣ ንጹህ እና ምቹ የሥራ አካባቢ ከመፍጠር አንጻር፣ በልህቀት አካዳሚው ግቢ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ሃገር በቀል እና ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል እና ተንከባክቦ በማሳደግ ለሌሎች አቻ ተቋማት አርአያ መሆን የሚችል ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በሁለተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ የተሳተፉ የልህቀት አካዳሚው ቤተሰቦች የችግኝ ተከላ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል፣ ብዝሀ ህይወትን ለመጠበቅ፣ የበረሀማነት መስፋፋትን ለመግታት እንዲሁም የላቀ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው በመሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ በመሳተፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
ነሐሴ 4 ቀን፣ 2012 ዓ.ም
የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ