እንደሚታወቀው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግስት የቴሌኮም ገበያን ለውድድር ክፍት ለማድረግ ባስቀመጠው እቅድ መሰረት ዘርፉን ለመምራት የኢትዮጵያ የኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣንን በማቋቋም በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 1148/2011 ባለስልጣኑ ከተሰጠው ስልጣን ውስጥ ጤናማ እና ውጤታማ የቴሌኮም ገበያ ውድድር እንዲኖር ማስቻል ዋነኛው ነው፡፡ በመሆኑም የሥልጠና ፕሮግራሙ የወጣዉን አዋጅና ባበለስልጣኑ ይፋ የተደረጉ መመሪያዎችን ኩባንያችን በአግባቡ ተፈፃሚ በማድረግ በደንበኞቹ ዘንድ ተመራጭና ተወዳዳሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስችል እና መመሪያዎቹ በአግባቡ ተግባራዊ ባይደረጉ ሊከተል የሚችለውን ተጠያቂነት ከወዲሁ ለመቀነስ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
የቨርቿል ሥልጠና ፕሮግራሙ የሬጉላቶሪ ግዴታዎች አፈጻጸምን ስለማጠናከር (“Improving Regulatory Compliance in Competitive Environment -IRCE)” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሲሆን የአቀራረብ ስልቱም ሠልጣኞች በሥራ ቦታቸው ሆነው በማይክሮሶፍት ቲምስ (MS Teams) በቪዲዮ ኮንፍራንስ መልክ በቀጥታ እንዲሳተፉ ማድረግ ያስቻለ ነው፡፡
የመጀመሪያው ዙር ሥልጠና በኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከወጡ 12 መመሪያዎች ውስጥ 4 ቱን ማለትም፡-
1-የቴሌኮሙኒኬሽን ተጠቃሚዎች መብት እና ጥበቃ መመሪያ ቁጥር 832/2013
2- የሲም ካርድ ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 799/2013
3-የቴሌኮሙኒኬሽን ውድድር መመሪያ ቁጥር 798/2013
4-የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጥራት መመሪያ ቁጥር 794/2013 ) እና የኮሙዩኒኬሽን አዋጅ ቁጥር 1148/2019
በሚዳስስ መንገድ የተቀረፀና የተሰጠ ሲሆን፣ ይህንኑ በሰፊው ለሌሎች ተጨማሪ ሰልጣኞች ማዳረስና ቀሪ መመሪያዎችንም እንደየቅደም-ተከተላቸው ለመስጠት ቀጣይ የስልጠና ፕሮግራም ለመቅረጽ ቅድመ-ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው፡፡
በመመሪያዎቹ ላይ የተጣሉት ግዴታዎች ተፈጻሚነትን ማረጋገጥ ከሚያስከትሉት ኃላፊነት እና የአገልግሎት ጥራት ማሻሻል አንጻር መሰረታዊ በመሆናቸው፣ ስልጠናው ለሁሉም የኢትዮ ቴሌኮም ቤተሰብ ተደራሽ ለማድረግ በቀጣይ በቨርቿል (Virtual)፣ በዲጂታል (self-learning)፣ በወርክሾፕ እና መመሪያዎቹን በተቋማችን ኢንትራኔት በማጋራት በሬጉላቶሪ መመሪያዎችና ሕጎቹ ላይ ግንዛቤን በማጎልበት ከድርጅታችን ማህበረሰብ የሚጠበቀውን ግዴታ የማስረጽ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡