በደም እጦት ህይወታቸው የሚያልፉ ወገኖቻችንን ለመታደግ እንዲቻል እና የማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንጻር እንዲሁም ከኮቪድ-19 መከሰት ጋር ተያይዞ እየተቀዛቀዘ የመጣውን የደም ልገሳ ባህል ለማስቀጠል በማሰብ የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ በቅጥር ግቢው ውስጥ ባስተባበረው የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ላይ የአካዳሚው፣ የክሊኒክ፣ የፊዚካል ሴኩሪቲ እና የዋናው እቃ ግ/ቤት እና ኢንቬንተሪ ማኔጅመንት ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በሙሉ በጎ ፍቃደኝነት የደም ልገሳ መርሃ-ግብሩ ላይ ከተለያዩ የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ ክፍሎች የተሳተፉ የስራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ደም መለገስ ምንም ተጓዳኝ የጤና ችግር የማያስከትል መሆኑን በመግለጽ ሌሎችም በዚህ የተቀደሰ ተግባር ላይ ተሳታፊ በመሆን ክቡሩን የሰው ህይወት በማዳን የሚገኘው የመንፈስ እርካታ እንዲጎናጸፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ በጎ ፍቃደኞች በቀጣይም በሚዘጋጁ መሰል የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል፡፡

በቋሚነት ደም በመለገስ ክቡሩን የሰው ሕይወት ይታደጉ!