የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ የስልጠና ፋሲሊቴተሮች ሰርተፊኬት አሰጣጥና የአፈጻጸም ግምገማ መርሀ-ግብር አከናወነ

የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ ለ121 የስልጠና ፋሲሊቴተሮች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አሰጣጥ ሥነ ስርዓት እና የ2012 በጀት ዓመት አጋማሽ የአፈጻጸም ግምገማ የካቲት 24 እና 25 ቀን፣ 2012 ዓ.ም አከናወነ፡፡ በፕሮግራሙ መክፈቻ የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ ቺፍ ኦፊሰር አቶ አየለ አዱኛ በ2012 በጀት ዓመት አጋማሽ አካዳሚው 9,991 ሰልጣኞችን በማሰልጠን በስልጠና አሰጣጥ ረገድ የዕቅዱን 115 በመቶ በማስመዝገቡ...