የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ ለ121 የስልጠና ፋሲሊቴተሮች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አሰጣጥ ሥነ ስርዓት እና የ2012 በጀት ዓመት አጋማሽ የአፈጻጸም ግምገማ የካቲት 24 እና 25 ቀን፣ 2012 ዓ.ም አከናወነ፡፡
በፕሮግራሙ መክፈቻ የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ ቺፍ ኦፊሰር አቶ አየለ አዱኛ በ2012 በጀት ዓመት አጋማሽ አካዳሚው 9,991 ሰልጣኞችን በማሰልጠን በስልጠና አሰጣጥ ረገድ የዕቅዱን 115 በመቶ በማስመዝገቡ እንዲሁም የስልጠና ፋሲሊቴተሮችን በማብቃት ረገድ የኩባንያው ከፍተኛ አመራር ጭምር የሚገኙበት 121 የስልጠና ፋሲሊቴተሮች ለሰርተፊኬት በመብቃታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በሰርተፊኬት አሰጣጥ መርሃ-ግብሩ ለአራት የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ብቁ በሆኑበት የስልጠና ፕሮግራሞች ሰርተፊኬት ከአቶ አየለ አዱኛ የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ ቺፍ የተቀበሉ ሲሆን ለቀሪዎቹ የስልጠና ፋሲሊቴሮች ደግሞ በከፍተኛ አመራር አባላቱ አማካኝነት ሰርተፊኬት ተበርክቷል፡፡
በሥነ ስርዓቱ ላይ አቶ አይናለም አልበኔ የፍሊት እና ፋሲሊቲ ቺፍ ኦፊሰር ባስተላለፉት መልዕክት በቴክኒካል፣ ኮሜርሻል፣ ሊደርሺፕ እና ትራንስቨርሳል ፕሮግራሞች የብቃት ሰርተፊኬት የተሰጣቸው የስልጠና ፋሲሊቴተሮች በስልጠና ወቅት ነባራዊውን የቴሌኮም ዘርፍ ተሞክሮ ለሰልጣኞች በማካፈል የአካዳሚው ፕሮግራሞች ከቢዝነሱ ጋር በማስተሳሰር ረገድ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም አሰልጣኞቹ ኩባንያው ሰው ተኮርና ዕውቀትን ያማከለ ተቋም ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ለማሳካት ተገቢውን የአሰልጣኝነት ሥነ-ምግባር በመላበስ የበኩላቸውን ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡