በኢትዮ ቴሌኮም የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ (ቴ.ል.አ.) እና የኢትዮ ሜዲካል ሰርቪስ የሥራ ክፍል ቤተሰቦች በደም እጦት ህይወታቸው የሚያልፍ ወገኖቻችንን ለመታደግ እንዲቻል እና እንደ ኩባንያ የማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የሚደረገው ጥረት አካል ለመሆን በአካዳሚው ቅጥር ግቢ የበጎ ፍቃደኞች የደም ልገሳ ፕሮግራም ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም. በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ፡፡
የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም የላቀ አስተማማኝ የኮሙኒኬሽን እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ለዜጎች በማቅረብ ህይወትን ለማቅለል እንዲሁም የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን ከሚያደርገው ጥረት ባለፈ ከህብረተሰቡ፣ ደንበኞች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን መስተጋብር ሰው ተኮር እንዲሆን ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት በተግባር የሚያስመሰክር ነው፡፡
በደም ልገሳ መርሃ-ግብሩ ላይ የተሳተፉ የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ እና የኢትዮ ቴሌኮም ሜዲካል ሰርቪስ የሥራ ክፍል ቤተሰቦች ደም መለገስ የሌሎች ህይወትን ለማስቀጠል የሚደረግ በጎ ምግባር መሆኑን በመግለጽ በዚህ የመንፈስ እርካታ በሚሰጥ ተግባር ላይ ተሳታፊ በመሆን ክቡሩን የሰው ልጅ ህይወት ለማዳን የበኩላቸውን ማድረግ በመቻላቸው የተሰማቸውን የመንፈስ እርካታ ገልጸዋል፡፡
የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ