የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የኩባንያችንን ‘መሪ የዲጂታል አገልግሎት አቅራቢ’ የመሆን ራዕይ እውን በማድረግ በኩል የLead 2025 የእድገት ስትራቴጂ ትግበራ ያለውን የማይተካ ሚና በመገንዘብ ትግበራውን ለማፋጠን፤ ምርታማነትን ለመጨመር እና የወጪ ልህቀት ባህል የማዳበር ሂደትን በተግባራዊ ተሳትፎ ለመደገፍ በታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ነፃ የሥራ ዘመቻ አከናወኑ፡፡
በአጠቃላይ በሥራ ዘመቻው የአካዳሚው የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በሙሉ ፍላጎት እና ንቃት ተሳትፈው በርካታ የLead 2025 የእድገት ስትራቴጂ ትግበራ እውን ለማድረግ የሚያግዙ ስራዎች አከናውነዋል፡፡
በሥራ ዘመቻው ወቅትም በተዘጋጀው የቡና ፕሮግራም አቶ አየለ አዱኛ የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ ቺፍ ኦፊሰር ባስተላለፉት መልዕክት የአካዳሚው ቤተሰቦች በዚህ ወሳኝ የውድድር ወቅት ‘‘አስተማማኝ የኮምዩኒኬሽን እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት በማቅረብ ህይወትን ማቅለል እና የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማፋጠን‘‘ እውን ለማድረግ፤ የኩባንያችንን የገበያ ድርሻ ለማሳደግ፣ የወጭ ልህቀትን ባህል ለማስፈን፤ ምርታማነትን ለመጨመር፣ የኦፕሬሽን ቅልጥፍናን ለማምጣት እና የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር መላው የአካዳሚው ቤተሰብ በሙሉ ቁርጠኝነት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡