ኢትዮ ቴሌኮም በደንበኞቹ ዘንድ ተመራጭና ተወዳዳሪ  የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ለመሆን ስትራቴጂ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ስትራቴጂው ከሰው ኃይል አቅም ግንባታ አንጻር  ግቡን እንዲመታ ለማስቻል የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ በሊደርሺፕና ማኔጅመንት፣ ቴክኒካል እንዲሁም ኮሜርሻል ስኩሎች አማካይነት ከሚሰጣቸው ሥልጠናዎች በተጨማሪ የሰፖርት ዶሜይን ሥራ ክፍሎችን አቅም በመገንባት ሚናቸውን በላቀ ሁኔታ እንዲወጡ ለማስቻል የሚሰራ የ “Support Functions School” ስራ ላይ አውሏል፡፡

አካዳሚው ትራንስቨርሳል የሆኑ የሰፖርት ሥራ ክፍሎችን ፍላጎት በመለየትና ፕሮግራሞችን በመቅረጽ ሥልጠናዎችን ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ይህን አሰራር ለማጎልበት ተግባራዊ ያደረገው የ “Support Functions School”  በሚሰጠው የመጀመሪያው ማዕቀፍ አማካይነት በፋይናንስ፣ የሰው ኃይል እና ሰፕላይ ቼይን ለሚገኙ የስራ ክፍሎች እንዲሁም በቴክኒካልና ኮሜርሻል ዲቪዥኖች ውስጥ የሚገኙ የሰፖርት ዶሜይን ሠራተኞችን ጨምሮ አቅም የመገንባት ዓላማ አንግቦ የሚሰራ ይሆናል፡፡

በዚህም መሰረት የ “Support Functions School” ሎጎ (ምልክት) የሚከተለው ይሆናል፡፡

TExA School Logos