የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ (ቴ.ል.አ) በሞባይል መኒ፣ በሊደርሺፕና ማኔጅመንት፣ በኮሜርሻል፣ በቴክኒካል እና በአድሆክ ሥልጠናዎች በአጠቃላይ 190 ከኦፕሬሽን እና ከቴ.ል.አ ለተመረጡና የማብቃት ሂደቱን በሚገባ ተከታትለው መስፈርቱን ላሟሉ የሥልጠና ፋሲሊቴተሮች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አሰጣጥ ሥነ-ስርዓት ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ አከናወነ፡፡
መርሃ-ግብሩ በአቶ አየለ አዱኛ፣ የቴ.ል.አ ቺፍ ኦፊሰር የመክፈቻ መልዕክት የተጀመረ ሲሆን በፕሮግራሙ በተገኙ ተጋባዥ የከፍተኛ ማኔጅመንት አባላት እና ተወካዮቻቸው አማካይነት መስፈርቱን ላሟሉ የሥልጠና ፋሲሊቴተሮች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተሰጥቷል፡፡
በዚሁ ዕለት በ International Youth Fellowship (IYF) አሰልጣኞች የአመለካከት ለውጥ (Mindset) ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን በመቀጠልም ቴ.ል.አ ከIYF ጋር በተለያዩ የአቅም ግንባታ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ፊርማ ሥነ-ስርአት ተከናውኗል፡፡
በዕለቱ ለኩባንያችን የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በነጻ በማከናወን ላይ ለሚገኙት Teach And Serve For Africa (TASFA) በዲጂታል ከ1500 በላይ ለሚሆኑ እና International Youth Fellowship (IYF) በገጽ ለገጽ ከ250 በላይ ለሚሆኑ የኩባንያችን ማህበረሰብ ሥልጠና በበጎ ፍቃድ በመስጠት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በመጨረሻም የሥልጠና ፋሲሊቴተሮችም ያገኙትን ዕውቀት በአግባቡ ለሰልጣኞች ለማስተላለፍ በጋራ ቃል-መሃላ የፈጸሙ ሲሆን በሰርተፊኬት አሰጣጥ ፕሮግራሙ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ