የቴ.ል.አ. የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የኩባንያችንን እና የአካዳሚውን የ2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም፣ የቀጣይ ሶስት ዓመት (2014-2016) ስትራቴጂ እና የ2014 በጀት ዓመት እቅዶች እንደየቅደም ተከተላቸው ቀርበው ሰፊ ውይይት የተካሄደባቸውና አመርቂ ግብዓቶች የተገኙበት ሲሆን፣ ተቋሙና ሠራተኞች ያስመዘገቡት የላቀ ውጤት ለቀጣይ በጀት ዓመት ስንቅ ሆኗቸው በመጪው የውድድር ጊዜ ተቋማችንን ቀዳሚና ተመራጭ ለማድረግ በጋራ  እንዲቆሙ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ከግብረ-መልሶች ለመረዳት ተችሏል፡፡

ውይይቱን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የከፈቱት የቴ.ል.አ. ቺፍ ኦፊሰር አቶ አየለ አዱኛ ሲሆኑ የዕለቱን መሪ መልዕክት “NEW BEGNININGS- Stay Strong, Move Forward with Positive Attitude &  Embrace a New Perspective!” ከህይወትና ከተቋሙ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ በበቂ ሁኔታ ያብራሩ ሲሆን በመቀጠልም በመርሃ-ግብሩ መሠረት ገንቢ የሆኑ ግብረ መልስና አስተያየት የተገኘበት እና እጅግ የተሳካ  ተወያዮችን ያስደሰተ፣ የይቻላል መንፈስ የፈጠረ መድረክ ሆኗል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች መድረኩ በተመሳሳይ ሁኔታ ጊዜ፣ ወጪንና በርካታ አቅርቦትን በመመደብ ሠራተኛው የተቋማችንን አፈጻጸምና የቀጣይ ጉዞ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኝና መዳረሻውን ተረድቶ ለአንድ ዓላማ እንዲቆም የሚያደርግ በመሆኑ ለተቋሙ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ይህ መሰል “Employees’ onboarding” ፕሮግራሞች እንደባህል ሆኖ እንዲቀጥል አስተያየታቸውን ሰጥቷል፡፡

በውይይቱ ላይ ከሰው ኃይል፣ ፋሲሊቲና ፍሊት፣ሰፕላይ ቼይን፣ ስትራቴጂና ፐርፎርማንስ ማኔጅመንት፣ ኢንፎርሜሽን ሲስተም እና ኢንፎርሜሽን ሴኩሪቲ ዲቪዥን ተወካይ ኃላፊዎችና የተገኙ ሲሆን በቴ.ል.አ. በኩል በቅድሚያ ተለይተው ለቀረቡ እና በመድረኩ ለተነሱ ለአካዳሚው የዕለት ከዕለት ኦፕሬሽን ተግዳሮት ለሆኑ ጉዳዮች የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡

የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ

ሐምሌ 2013 ዓ.ም