የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ ማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች ነጻ የሥራ ዘመቻ ቅዳሜ ታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ በዕለቱም ዕድሳት ተደርጎለት በአዲስ መልክ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን ቤተመጽሐፍት አስመልክቶ የቡና ፕሮግራም የተዘጋጀ ሲሆን ቀደም ሲል በአካዳሚው ምስረታ ላይ ለተሳተፉ የእዉቅና ሰርተፊኬት አሰጣጥ መርሃ ግብርም ተከናውኗል፡፡
በነጻ የሥራ ዘመቻው ወቅት የተለያዩ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ለተለያዩ የገጽ-ለገጽና ዲጂታል ሥልጠናዎች የፕሮግራም የንድፈ-ሃሳብ (concept map)፣ አጠቃላይ ዕይታ (program overview) እና ስክሪፕት ማዘጋጀት፣ የአዳዲስ ሥልጠና ፕሮግራሞች ይዘት ዝግጅት ግብዓት መረጃ ማሰባሰብና መለየት፣ ለዲቪዥኖች የስልጠና ፕሮግራም ካታሎግ ማዘጋጀት፣ስለቬንደር (ZTE, Huawei & Ericsson) የቴሌኮም መሣሪያዎች (vendor specific equipment) በራስ አቅም የሚዘጋጁ ስልጠናዎችን መለየት እና ዕቅድ ማዘጋጀት፣ ከባለድርሻ አካላት በተሰጡ ግብዓቶች መሠረት የስልጠና ፕሮግራሞችን የማትባት፣ በቤተሙከራዎች የሚገኙ የቴሌኮም መሣሪያዎች መፈተሽና ወቅታዊ መረጃ የመያዝ፣ የአሰልጣኞችን ምልመላ ሪፖርት ማዘጋጀትና ብቁ የሆኑ አሰልጣኞችን ዝርዝር የማሳወቅ፣ የገጽ-ለገጽ የሰልጣኞች ዝርዝር ቋት ማጥራት፣ ወደ ዲጂታል ሥልጠና ለመቀየር የሚችሉ የገጽ-ለገጽ የሥልጠና ፕሮግራሞችን መለየትና የቀጣይ ትግበራ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት፣ ለዲጂታል ሥልጠናዎች ቪዲዮዎችን ማዘጋጀት፣ ለዲጂታል የሥልጠና ፕሮግራሞች የተጋባዥ ሠልጣኞች ዝርዝር የማዘጋጀት፤ ለዲጂታል ሠልጣኞች ድጋፍ የመስጠት፣ የጊዜያዊ የዲጂታል ስቱዲዮ ሥራ ድጋፍና ክትትል፣ የሰልጣኞች ደረጃ አንድ ጥናት ግብረ-መልስ ትንተና፣ የሥልጠና በስራ ላይ የመተግበር መጠን የዳሰሳ ጥናት ሪፓርቶችን ከሲስተም በማውጣት ለጥናቱ ምላሽ ላልሰጡ የስራ ሃላፊዎች ማስታወሻ የመላክ፤ መጠይቆችን የማሻሻልና ለተሳታፊዎች የመላክ፣ የሶስተኛ ሩብ ዓመት የስልጠና ዕቅድ ማዘጋጀት የግማሽ ዓመት ሪፖርት ቅድመ ዝግጅት፣ ለኢ-ላይብረሪ ግንባታ የመስፈርት ዝግጅት፣ በአካዳሚው የሚገኙ የሥልጠና ክፍሎችን፣ ቤተ-ሙከራዎች፣ መጋዘን እና በአጠቃላይ ቅጥር ግቢውን በመጎብኘት አገልግሎት የማይሰጡ ቁሰቁሶችን በመለየት ወደ ዋናው ግምጃ ቤት የመላክ ፣ ለሙዚየም የሚሆኑ ጥንታዊ ዕቃዎች የማሰባሰብ እንዲሁም የአዳዲስ ምክረ ሃሳቦችን የማዘጋጀት እና ሰባት ለሚሆኑ ለተከለሱ የሥራ ሂደቶች መግለጫ የማዘጋጀት ስራዎች ተከናውኗል፡፡
የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ ማኔጅመንት አባላት የሥራ ዕቅድ በማውጣትና በዕለቱ በመገኘት ድጋፍና ክትትል በማድረግ የነጻ ሥራ ዘመቻውን ያስተባበሩ ሲሆን ሠራተኞቹ ያካሄዱት የአንድ ቀን ነፃ የሥራ ዘመቻ በትርፍ የሥራ ሰዓት ክፍያነት ሲታሰብ ከ241,865.68 ብር በላይ የሚገመት ወጪ ለማዳን ተችሏል፡፡
የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ