ከ1000 በላይ ለሚሆኑ የሃይብራይድ ዲዛይን .የተ.የግ.. (ራይድ) አሽከርካሪዎች ስትራቴጂክ አጋርነትን ለማሳደግ የሚያስችል ሥልጠና ተሰጠ

 

ኢትዮ ቴሌኮም በደንበኞቹ ዘንድ ተመራጭ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ለመሆን በሚያደርገው ጥረት ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ጋር በማድረግ ላይ ያለውን ስትራቴጂካዊ ትስስር በማጠናከር ላይ መሆኑን ተከትሎ ኩባንያችን ከሃይብራይድ ዲዛይን ኃ.የተ.የግ.ማ. ጋር ያደረገውን ስትራቴጂካዊ አጋርነትን በክህሎት ለማገዝ ይቻል ዘንድ የድርጅቱ ሠራተኞችና ራይድ አሽከርካሪዎች በማስተር ኤጀንትነትና ኤጀንትነት የሲም ካርድ፣ የቴሌ ብር እንዲሁም ሌሎች የቴሌኮም ምርትና አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ሥልጠና በኢትዮ ቴሌኮም ተሰጠ፡፡

 

 

 

 

በቅድመ ስልጠና ፕሮግራሙ መርሃ ግብር መሠረት ሰላሳ (30) የሚሆኑ ባለሙያዎች የስልጠናውን የአሰልጣኞች ስልጠና ፕሮግራም በመስጠት ቀጥሎም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ 250 በላይ ለሚሆኑ ራይድ አሽከርካሪዎች  Ethio telecom – Hybrid Designs Strategic Partnership የተሰኘ የአንድ ቀን ስልጠና በአምስት  ዙር የተሰጠ ሲሆን  የስልጠና ፕሮግራሙ በቀጣይ መርሃ ግብር በከተማቸን የሚገኙ የራይድ ተጨማሪ አሽከርካሪዎችን ለማሰልጠን ዕቅድ ተነድፎ በትግበራ ላይ ይገኛል፡፡

ስልጠናው የኢትዮ ቴሌኮምን ስትራቴጂ ማዕቀፍና እና ትልም (aspiration) ታሳቢ በማድረግ፣ ለደንበኞች ተደራሽ ለመሆን – የስትራቴጂክ አጋርነት የማይተካ ሚና ያለው በመሆኑ የሞባይል መኒ አገልግሎትን ሥነ-ምህዳር፣ የቴሌ ብር ማስተር ኤጀንት እና ኤጀንቶችን ተግባር ፣ የቴሌ ብር አገልግሎት መሰረታዊ ግብይቶችን እና የእሴት ምክረ ሃሳብ (value proposition)፣ የሽያጭ አገልግሎትና የደንበኞች አያያዝ ክህሎቶች አካቶ በአጠቃላይ ስለሞባይል ገንዘብ ዓለም አቀፋዊ ሥነ-ምህዳር ግንዛቤን ጭምር ለመፍጠር ያለመ ነው።

የስልጠና ፕሮግራሙ የሃይብራይድ ዲዛይን ኃ.የተ.የግ.ማ. ሠራተኞችና የራይድ አሽከርካሪዎች የሲም ካርድ ሽያጭ፣ በቴሌ ብር አገልግሎት አማካይነት ክፍያ መፈጸም፣ ገንዘብ መቀበል፣ ማስተላለፍ፣ የአየር ሰዓትና ጥቅል አገልግሎት መግዛት፣ ትኬት መግዛት፣ ስጦታ መላክ፣ ከውጭ ሃገር ገንዘብ መቀበል፣ ለበጎ አድራጎት ተግባራት ገንዘብ መለገስ እና ሌሎችም የግብይት አገልግሎቶች በመጠቀም፣ በማስተዋወቅና በወኪልነት በመስራት ኩባንያችን የሀገራችንን የፋይናንስ ግብይት ዲጂታል ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት የበኩላቸውን ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ ያስችላል፡፡

በመጨረሻም ሥልጠናውን የወሰዱ ሰልጣኞች ስልጠናው የቴሌ ብርን እና ሌሎችም የኢትዮ ቴሌኮምን ምርትና አገልግሎቶችን በመረዳት በወኪልነት ለመስራት የሚያስችላቸውን መሠረታዊ ዕውቀት እንደገበዩ እና በሥልጠናውም በሚገባ የረኩ መሆናቸውን በመግለጽ በአጠቃላይ ለተቋማችን፣ በተለይም በስልጠናው ዙሪያ ለተሰማሩት አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ህዳር 2014 ዓ.ም