ኢትዮ ቴሌኮም በመላው ሀገራችን እየሰጠና ወደፊት የሚሰጣቸውን የቴሌኮምና ፋይናንስ (ቴሌብር) ምርት እና አገልግሎቶቹን እና ማዕከላትን  ለደንበኞች በስፋት፣ በጥራት እና በቅልጥፍና በማዳረስ ጥራት ያለው አማራጭ አገልግሎቶቹን በተመደቡበት የአገልግሎት አካባቢ በላቀ መልኩ በመስጠት፤ የደንበኞች ተሞክሮና እርካታ በመጨመር እና በጋራ ስኬት ውስጥ በገበያው አንደኛና ተመራጭ ሆኖ ለመገኘት የሚያስላቸውን የይቻላል አመለካካት፣ መርህ፣ ልምድ፣ ከደንበኞችና ተቋማችን የሚጠበቁትንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚያመላክት መንገድ በሽያጭ፣ የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ እና በሰው ኃይል ዲቪዥኖች   “Enhancing Distribution Channel in Competition Market” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የሥልጠና እና የምክክር መርሀ-ግብር በቅርቡ በብቸኛ አጋርነት (exclusive strategic partnership) እና ሴሌክቲቭ አከፋፋዮች በመሆን በአጋርነት ለመስራት ስምምነት ለፈጸሙ ድርጅቶች ከግንቦት 4-12 ቀን 2014 ዓ.ም.  በአካዳሚያችን በስኬት ተከናወነ፡፡

በዚሁ የሥልጠና እና የምክክር መርሀ-ግብር በሰባት ዙር 246 ለሚሆኑ ብቸኛ (exclusive) ሃገራዊ እና የሪጅን አከፋፋዮች እንዲሁም ሴሌክቲቭ አከፋፋይ ባለቤቶች፣ ማኔጅመንቶች እና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎቻቸው የተሳተፉ ሲሆን  ፕሮግራሙ በውድድር ገበያ ውጤታማ ለመሆን የሚያስችሉ ስለቴሌኮም እና የፋይናንስ ገበያ፤ በቢዝነስ ዓለም የአሸናፊነት ባህርይን ስለመላበስ፤ ስለአጋር የስርጭት ቻናል ጠቀሜታ፤ ስለስርጭት ቻናል አስተዳደር እና ውጤታማነት፤ የቴሌኮም ምርት እና አገልግሎት ፖዚሽኒንግ፤ የደንበኞችን መልካም ተሞክሮ ስለማሳደግ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ሥነ ምግባር እና የቁጥጥር ደንቦችን ማክበርን የተመለከቱ እና ሌሎች ተያያዥ ይዘቶችን ያካተተ ሲሆን በአጠቃላይ አከፋፋዮች የገበያ ተወዳዳሪነትና ተመራጭነትን ለማረጋገጥ የሚያስችላቸውን እውቀት እና ክህሎት እንዲያዳብሩ የሚያደርግ ነው፡፡

በሥልጠና እና ምክክር ፕሮግራሞቹ መክፈቻ እና መዝጊያ ላይ አቶ መሐመድ ሃጂ ቺፍ ሴልስ ዲቪዥን ኦፊሰር፣ አቶ አየለ አዱኛ ቺፍ የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ ኦፊሰር  እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው የኩባንያችን ከፍተኛ አመራሮች በመገኘት መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በዚህም ወቅት ኢትዮ ቴሌኮም በተለይ ባለፉት ሶስት አመታት የውድድር ገበያን ግምት ውስጥ በማስገባት በደንበኞቹ ዘንድ ተመራጭ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ መሆን የሚል ራዕይን አንግቦ በርካታ መዋቅራዊ፣ የቴክኖሎጂ እና የአሰራር ለውጦችን ማከናወኑን በመግለጽ በተመሳሳይም ከአከፋፋዮች ጋር ከመቼውም በላይ የላቀ አጋርነት ለመፍጠር እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን በመግለጽ አከፋፋዮችም በተመሳሳይ የውድድር ገበያን ግምት ውስጥ በማስገባት በደንበኞቻቸው እና በአጋሮቻቸው ዘንድ ተመራጭ ለመሆን ስትራቴጂ እና የቢዝነስ ዕቅድ አውጥተው ምርት እና አገልግሎታችንን በተቀመጠው አሰራር መሠረት ተደራሽ የማድረግ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት በታሪክ አጋጣሚ የተሰጣቸውን የሀገር ኩራት ከሆነው ኩባንያ ጋር በአጋርነት የመሥራት እድል በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው ከመድረኩ በአጽንኦት ተገልጾላቸዋል፡፡

በሁሉም ፕሮግራሞች ማጠናቀቂያ ላይ ተሳታፊዎች በሰጡት ግብረ መልስ የስልጠናውን ዝግጅት እና አቀራረብ በማድነቅ በቆይታቸው ያገኙትን ግንዛቤ እና ተሞክሮዎች በመተግበር የቴሌኮም ምርት እና አገልግሎቶችን በቅልጥፍና ለህብረተሰቡ የማድረስ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በቁርጠኝነት፣ በቀናነት፣ በታማኝነት እንዲሁም የስርጭት ሥራ የሚፈልገውን ሥነምግባር በማክበር እና እጅ ለእጅ በመያያዝ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎሜሽን እና ሁለንተናዊ እድገት ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ  የበኩላቸውን ሚና በቁርጠኝነት እንደሚወጡ ቃል መግባታቸውን በፊርማ አረጋግጠዋል፡፡